በበቴ ዑርጌሳ የግድያ ምርመራ ላይ ስጋት እንዳለው ኦነግ አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የኦነግ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት የአቶ በቴ ዑርጌሳ ግድያን ተከትሎ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እየተካሔደ ባለው የምርመራ ሒደት ላይ ስጋት እንዳለው ኦነግ አስታውቋል።

ግንባሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ለግድያው የመጀመሪያ የዐይን ምስክር የኾኑ ሰዎች ደብዛቸው እንዲጠፋ በመደረግ ላይ ናቸው፤ ሲል ገልጾ ግድያው በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ዳግም ጥሪ አቅርቧል።

በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት አካላት ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።