በዌስት ባንክ የጠፋው እስራኤላዊ ዐዳጊ ሞቶ መገኘቱን ኔታኒያሁ አስታወቁ

በእስራኤል ቁጥጥር ስር የሚገኘው ዌስት ባንክ

በእስራኤል ቁጥጥር ስር የሚገኘው ዌስት ባንክ

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሁ በእስራኤል ይዞታ በሚገኘው በዌስት ባንክ ጠፍቶ የነበረው እስራኤላዊ ዐዳጊ ‘አሰቃቂ’ ሲሉ የጠሩት ግድያ ተፈጽሞበት አስክሬኑ መገኘቱን አስታውቀዋል። የ14 ዓመቱ ቤንጃሚን አቺሚየር ትላንት አርብ መጥፋቱ ከታወቀበት ሰዓት አንስቶ የፍልስጤም መንደሮችን ላይ ከፍተኛ የሆን ጥቃትን ያስከተለ ሰፊ የሆነ የፍለጋ ዘመቻ ተካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ “ልጁ በአሰቃቂ ሁኔታ በመገደሉ...ወንጀሉ ከባድ ነው” ሲሉ በመግለጫቸው አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም የእስራኤል ሃይሎች “ይህንን አሰቃቂ ወንጀል የፈጸሙትን እና የተባበሩትን ለመፈለግ በጽኑ እየጣሩ ነው” ብለዋል።

የዐዳጊው ልጅ መጥፋት ከታወቀበት ሰዓት አንስቶ የእስራኤል የጸጥታ ሃይሎች ከ100 በጎ ፍቃደኞች ጋር በመሆን ለፍለጋ የተሰማሩ ሲሆን አል-ሙግሃየር መንደርን ጥሰው መግባታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። በክስተቱ 25 ሰዎች ሲጎዱ አንድ ሰው መገደሉን የፍልስጤም የጤና ሚኒስትር አስታውቋል።