ያለፍትሕ ታስረው የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባሎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ አራት ፓርቲዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል፡፡
ከፓርቲዎቹ አንዱ የኾነው የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር መጋቤ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት፣ ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በኋላ በፓርቲዎች ላይ የሚደርሰው ጫና መባባሱን ተናግረዋል፡፡
የእናት ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሰይፈ ሥላሴ አያሌው ደግሞ፣ ይህ አካሔድ “በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ላይ ዕንቅፋት ይኾናል፤” ብለዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ፣ ከመንግሥት በኩል ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ሊሳካልን አልቻለም፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።