የአሜሪካ 'አፈርማቲቭ አክሽን' መቀልበስ በተማሪዎች ላይ ምን ተፅእኖ አለው?

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ጥቁሮችን፣ ሴቶችን እና ሌሎች አናሳ የማህበረሰብ ክፍሎችን ጨምሮ፣ በአሜሪካ የሀብት ድልድል ተካፋይ ያልሆኑ ወይም አድልዎ ተደርጎባቸዋል ተብለው የሚታሰቡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን ዘርን ያገናዘበ መመልመያ ፖሊሲ (አፈርማቲቭ አክሽን) ከዚህ በኃላ ተፈፃሚ እንዳይሆን ውሳኔ ካሳለፈ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩንቨርስቲዎች አዲስ ተማሪዎችን ወደ ተቋማቸው እየተቀበሉ ነው።

በርዕዮተ ዓለም መስመር የተከፋፈሉት የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድቤት ዳኞች ስድስት ለሶስት በሆነ ድምፅ፣ ላለፉት 45 አመታት በስራ ላይ የኖረውን ፖሊሲ መቀየራቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚኖረው የትምህርት ዕድል እና የዘር ስብጥር ላይ ምን አይነት ተፅእኖ ይኖረዋል ስትል፣ ስመኝሽ የቆየ በሚኖሶታ የከተማ ምክር ቤት የፍትሃዊነት እና የእኩል ዕድል ቢሮ ረዳት ዳይሬክተር የሆኑትን የህግ ባለሙያ አቶ ዘካሪያስ ሀይሉ አነጋግራቸዋለች።