በማይፀምሪ በተካሔደ ሰልፍ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እንዲከበር ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እንዲከበር የሚጠይቅ ሰልፍ፣ በምዕራብ ጠለምት ወረዳ እና ማይፀምሪ ከተማ መካሔዱን፣ የአሜሪካ ድምፅ በስልክ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለጹ።

ነዋሪዎቹ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከትግራይ ክልል በኩል ተሰንዝሯል ያሉት ጥቃት እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል።

ቀደም ሲል ባሳለፏቸው ጦርነቶች ግጭቶች እንዲያበቁ፣ ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ፣ ራስን በራስ የማስተዳደርና የማንነት ጥያቄዎቻቸውም ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል፣ ሰልፉ በግዳጅ የተካሔደ ስለመኾኑ፣ በማይፀምሪ ከተማ የሚኖሩ አንድ የትግራይ ክልል ተወላጅ ተናግረዋል። ክሱን የማይፀምሪ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት “ሐሰት” ሲል አጣጥሎታል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።