ከተጀመረ ስድስት ወራት የሞሉት የእስራኤል ሀማስ ጦርነትን ለማሸነፍ ተቃርበናል ሲሉ ዛሬ እሁድ ኔታኒያሁ አስታወቁ። ፕሬዘዳንቱ ይሄንን ያሉት በደቡባዊ ጋዛ ‘በቂ ሃይል’ አስቀርተው የተቀረ ሃይላቸውን ካስወጡ በኋላ ነው።
ፕሬዘዳንቱ ለካቢኔያቸው ባደረጉት ንግግር “ለድል አንድ እርምጃ ይቀረናል” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “ይሁን እንጂ የከፈልነው መስዋዕትነት የሚያሰቃይ እና ልብ ሰባሪ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ምንም እንኳን በካይሮ የተኩስ አቁም ድርድር እየተደረገ ቢሆንም ፕሬዘዳንቱ “ታጋች ዜጎቻቸን ካልተመለሱ በፍጹም የተኩስ አቁም አይኖርም” ሲሉ ቃል ገብተዋል።
ሀማስ በጋዛ ስርቻዎች ውስጥ 100 የሚሆኑ የቆዩ ታጋቾችን እና በጎሮጎርሳዊያኑ ጥቅምት ሰባት 1200 ሰዎችን ገድሎ 250 የሚሆኑ ታጋቾችን እንደያዘ ነው። በጋዛ የሚመራው የሀማስ የጤና ሚኒስቴር እስራኤል በፈጸመችው የመልሶ ማጥቃት 33,000 ሰዎችን መግደሏን እና ከእነዚህ ውስጥ ሁለት ሦስተኛዎቹ ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውን አስታውቋል።