የእርሻ መሬት ለሥራ ዐጥ ወጣቶች እንዲሰጥ የሚጠይቅ ሰልፍ በራያ አዘቦ ተካሔደ

Your browser doesn’t support HTML5

በራያ አዘቦ ወረዳ መኾኒ ከተማ፣ “መሬታችን በኢንቨስትመንት ስም ለማያለሙ ባለሀብቶች እየተሰጠ ልጆቻችን ሥራ አጥ ኾኑ፤” ያሉ አርሶ አደሮች የተቃውሞ ሰልፍ አካሔዱ።

ትላንት ሰኞ ሰልፍ የወጡት አርሶ አደሮቹ፣ የእርሻ መሬት ማግኘት የሚገባቸው ወጣቶች ለስደት መዳረጋቸውን ባሰሟቸው መፈክሮች አመልክተዋል። በጉዳዩ ላይ፣ ከከተማው እና ከዞኑ አመራሮች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።