በኤፍራታ ግድም ታግተዋል የተባሉ ግብርና ጽ/ቤት ሠራተኞች እንዲለቀቁ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊን ጨምሮ ከሁለት ወራት በፊት ታግተዋል ያሏቸው አራት የመንግሥት ሠራተኞች እንዲለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ጠየቁ። ግለሰቦቹ የታገቱት በፋኖ ታጣቂዎች መሆኑን የቤተሰብ አባላት ለቪኦኤ ተናግረዋል።

እገታው መፈጸሙን ያረጋገጡት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብደላ አሕመድ፣ አባ ገዳዎች እና የአገር ሽማግሌዎች ለማስለቀቅ እየጣሩ መሆኑን እንደሚያውቁም ተናግረዋል።

ከፋኖ ታጣቂዎች እና ከአማራ ክልል መንግሥት ምላሽ እና አስተያየት መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።