“የሰቆጣ ቃል ኪዳን” በአማራ እና በትግራይ ወቅታዊ ችግሮች ሳቢያ ሳንካ ገጥሞታል

Your browser doesn’t support HTML5

በሀገር አቀፍ ደረጃ በአጣዳፊ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ወይም መቀንጨር የተጎዱ ሕፃናትን ለመታደግ የተጀመረው ሥራ፣ በተለይ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ባሉ ወቅታዊ ችግሮች ዕንቅፋት እንደገጠመው፣ የሰቆጣ ቃል ኪዳን /ሰቆጣ ዲክላሬሽን/ ፕሮግራም አስታወቀ፡፡

በጤና ሚኒስቴር የሰቆጣ ዲክላሬሽን ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ፍሥሓ ተክሌ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በኢትዮጵያ ዕድሜአቸው ከአምስት ዓመት በታች ከኾኑ ሕፃናት መካከል፣ ከስድስት ሚሊዮን ያላነሱት፣ “መቀንጨር” ወይም አጣዳፊ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዳለባቸው በጥናት መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡

ጉዳቱ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ሥር ሰዶ እንደሚገኝ ያመለከቱት የፕሮግራሙ አስተባባሪ፣ ኾኖም በአማራ ክልል የጸጥታ ችግር እና በትግራይ ክልል ደግሞ መንግሥታዊ መዋቅሩ እስከታች ድረስ በአግባቡ ሥራ ባለመጀመሩ ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።