በምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች፣ በጊዳሜ እና በቤጊ ወረዳዎች በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች፣ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት፣ ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በደኅንነት ስጋት ስማቸው እንዳይጠቅስ የጠየቁ የሁለቱ ወረዳዎች ነዎሪዎች፣ በቁጥር 16 እንደኾኑ የገለጿቸው ሰዎች የተገደሉት “በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ነው፤” ሲሉ ወንጅለዋል።
ነዋሪዎቹ ባነሡት ቅሬታ ላይ፣ ከሁለቱ ዞኖች እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።
የአገሪቱ ወታደራዊ እና ሲቪል ባለሥልጣናት በቅርቡ በሰጧቸው አስተያየቶች፣ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊትም ኾነ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች በአጠቃላይ፣ ሲቪሎችንም ኾነ የሲቪል ተቋማትን ዒላማ አያደርጉም፤ ሲሉ መሰል ውንጀላዎችን ተከላክለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።