በዶዶላ ከተማ ጥቃት 11 አገልጋዮች እና ምእመናን ተገደሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ፣ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ምሽት፣ በታጣቂዎች እንደተፈጸመ በተገለጸ ጥቃት 11 ሰዎች መገደላቸውን፣ የዶዶላ ከተማ አስተዳደር ገልጿል።

ጥቃቱ፣ በዶዶላ ከተማ ደነባ ክፍለ ከተማ በደብረ ቅዱሳን ጻድቁ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መፈጸሙን ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት የዶዶላ ከተማ ኮምዩኒኬሽንስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማን ዳቤ፣ “በመኖሪያ ቤታቸው የነበሩ 11 ሰዎች ተገድለዋል” ብለዋል። ግድያውን አስመልክቶ ዛሬ ረቡዕ መግለጫ ያወጣው እናት ፓርቲ፣ “መንግሥት አሁንም የዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ አልቻለም” ሲል ተችቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።