አዲስ አበባ እና አካባቢው በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ የተባሉ 50 ሰዎች ታሰሩ

ፎቶ ፋይል - አዲስ አበባ ከተማ

በአዲስ አበባ እና አካባቢው በትጥቅ የታገዘ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ነበሩ የተባሉ 50 ሰዎች መታሰራቸውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል ከፎቷቸው ጋራ በማጋራት አስታውቋል።

ግብረ ኃይሉ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሃምሳዎቹ ተጠርጣሪዎች፣ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ካላቸውና “ፀረ ሰላም ኃይል” ሲል ከገለጻቸው አካላት ጋራ የህቡዕ ትስስር አላቸው በማለትም አክሏል። የታሳሪዎቹን ማንነት ለማጣራት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ ጉዳዩን ከመግለጫው መስማቱን አስታውቋል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ከቤተሰብ አባላት የደረሳቸው መረጃ ኮሚሽኑ ገልጿል። ፡በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት አካል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Your browser doesn’t support HTML5

አዲስ አበባ እና አካባቢው በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ የተባሉ 50 ሰዎች ታሰሩ