የትግራይ ክልል ጡረተኞች ውዝፍ አበል እንዲከፈል ተወሰነ

Your browser doesn’t support HTML5

የፌደራሉ መንግሥት፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ለወራት ተቋርጦ የቆየው የትግራይ ክልል ጡረተኞች ውዝፍ አበል እንዲከፈል መወሰኑን፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ደ’ኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ አስታወቁ።

የጡረታ መዋጮ ባልተሰበሰበበት ኹኔታ ጡረታ እንዲከፈል የሚፈቅድ አሠራር ባይኖርም፣ በፖለቲካ ውሳኔ እንዲፈጸም መታዘዙን ሚኒስትር ደ’ኤታው ገልጸዋል፡፡ በውሳኔው መሠረት፣ የመንግሥትም ኾነ የግል ተቋማት ጡረተኞች ለአንድ ዓመት ከመንፈቅ ያህል የተቋረጠ አበላቸውን በቀጣዮቹ ሳምንታት እንደሚያገኙ ተገልጿል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የመቐለ ከተማ ጡረተኞች፣ የዘገየ ውሳኔ ቢኾንም በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲደረግ ጠይቀዋል።