ሴት የፖለቲካ እስረኞች

Your browser doesn’t support HTML5

ሎስ አንጀለስ የሚኖሩ ሩስያውያን አገር ቤት ላሉ ሴት የፖለቲካ እስረኞች ደብዳቤ እየጻፉ ነው። ከብዙ ዓመታት በፊት 'ፑሲ ራየት" በሚል ስያሜ ለሴቶች መብት አቀንቃኝ ሴት ሙዚቀኞች ቡድን መስራቿ ናዲያ ቶሎኮኒንኮቫ ትባላለች። ናዲያ በሩሲያ ወህኒ ቤት ለአንድ ዓመት ከአራት ወር ለእስር ተዳርጋለች።

ሴቶች በፖለቲካ ተቃውሞ ምክንያት ለእስር ሲዳረጉ ለተጨማሪ ወከባ እንደሚጋለጡ ትናገራለች። ዩናይትድ ስቴትስ ሎስ አንጀለስ ከተማ የሚኖሩ የሩሲያ ተወላጆች ታዲያ በትውልድ ሀገራቸው በፖለቲካ ምክንያት ለታሰሩ ሴቶች " አብረናችሁ ነን" በማለት ደብዳቤ ጽፈውላቸዋል።

የቪኦኤው ስቲቭ ባራጎና ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።