አርሶ አደሮች በዘንድሮውም መኸር የግብአት አቅርቦት ላይ ስጋታቸውን ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

በዘንድሮው የመኸር እርሻ በቂ የምርት ግብአቶችን በወቅቱ ላያገኙ እንደሚችሉ ያመለከቱ አርሶ አደሮች፣ በአቅርቦቱ ላይ ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል፡፡

ባለፈው መኸር ያጋጠመውን የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ያወሱና ዘንድሮም ሊደገም እንደሚችል የጠቆሙ አንድ የንግድ እና ምጣኔ ሀብት ባለሞያ፣ “ሁኔታው የምርት እጥረትን ያስከትላል፤ ውጤቱም የኑሮ ውድነቱን የበለጠ አስከፊ ያደርገዋል፤” ሲሉ አመልክተዋል።

የግብርና ሚኒስትሩ ግን፣ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትን ጨምሮ አስፈላጊ የምርት ግብአቶችን በጊዜው ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን ለአገር ውስጥ ብዙኃን መገናኛ በቅርቡ ተናግረዋል።