የፊልም አቀናባሪዎቹ እንግሊዛዊዋ ኤማ ቶማስ፣ አሜሪካዊው ቻርለስ ሮቨን፤ እንዲሁንም እውቁ ፊልም ሠሪ ክሪስቶፈር የፊልም አቀናባሪ ኖላን ‘ኦፕንሃይመር’ በተባለው ፊልማቸው በ96ኛው ዓመታዊ የፊል አካዳሚ ሽልማት በሆሊውዱ ዶልቢ የቴአትር መድረክ ለዓመቱ ምርጥ ሲኒማ የተዘጋጀውን ሽልማት በጋራ ተቀብለዋል።
ድፍን ሦስት ሰአታት የሚዘልቀው እና የአንድን ሰው ህይወት የሚተርከ፤ ከዓለም ዙሪያ የፊልም ተመልካቾች የቢሊየን ዶላር የሚያዝቅ ስሜት ሰቅዞ የሚይዝ ሲኒማ ይወጣዋል ተብሎ ያልተጠበቀው ‘ኦፕንሃይመር’ በ96ኛው የአካዳሚ ሽልማቶች መድረክ ለክርስቶፈር ኖላን ድርብ የክብር ዘውድ የጫነ ሆኗል።
በግዙፉ የሲኒማ ስክሪን ለዕይታ ባበቃቸው ተወዳጅ ፊልሞቹ ከፍተኛ አድናቆት ቢያተርፍም፣ ለዓመታት ሽልማት ሳያገኝ የቆየውን ስመ ገናና የፊልም ሰሪ፡ ለመሪ ተዋናዩ ሲሊያን መርፊ የዓመቱን ኮከብ ሽልማት፣ ሮበርት ዳውኒ ጁኒየርን የምርጥ አጋር ተዋናይ ሽልማት እና ኖላን’ን ራሱን ደግሞ የምርጥ ዳይሬክተር ተሸላሚ ያደረገበትን ጨምሮ፡ ‘ኦፐንሃይመር’ን በሰባት ልዩ-ልዩ ሽልማቶች በማንበሽበሽ፤ ኖላን ካሁን ቀደም ያመለጡትን ሽልማቶች ሁሉ አካክሶታል።
‘ኦፕንሃይመር’ በሽላማቶች ያደመቀው የሲኒማ ጥበባዊ ሥራዎች እና የሳይንስ አካዳሚ - ኦስካር ባለፉት ከአሥር ዓመታት በላይ በሚሆን ጊዜ ውስጥ አድርጎት የማያውቅ አንድ ሌላ ነገርም ፈጽሟል። ትልቁን የዓመቱን ሽልማት በሥፋት ለታየ እና ግዙፍ በጀት ለጠየቀ የስቱዲዮ ፊልም ነው የሰጠው።
የፊልም ትኬት መሸጫ ኪዮስኮች እንዲጨናነቁ፣ የፊልም ኢንዱስትሪው ለወትሮው የዳይኖሰር ታሪክ ያለበት አሊያም ቶም ክሩዝ የሚጫወባቸውን የመሰሉ በልዩ እንቅስቃሴ የታጀቡ ፊልሞች ያደርጉ እንዳልነበር ዘንድሮ ግን የኒዩክሌር ሽብልቅ የሚታይበት፣ የጄ ሮበርት ኦፐንሃይመርን የህይወት ታሪክ ድራማ እና የአቶሚክ ቦምብ ስሪት የሚተርክ ረቂቅ ሲኒማ ተመልካቾችን ወደ ሲኒማ ቤቶች አጉርፏል።
"በጎም ይሁን ክፉ፣ ሁላችንም በሮበርት ኦፔንሃይመር ዓለም ውስጥ ነው የምንኖረው" ያለው የፊልሙ መሪ ተዋናይ መርፊ ሽልማቱን በተቀበለበት ወቅት ባሰማው ንግግር “ይህንን ሽልማት ለሰላም ፈጣሪዎች ክብር እንዲሆን እሻለሁ” ሲል አክሏል።
እንደ ፊልም የሰውን ልጅ የጅምላ ፍጅት የማድረስ .. ‘ጥሩ ስሜት እንዳይሰማን የሚያደርግ’ .. አቅም የሚያሳየው ‘ኦፕንሃይመር’ .. እንዲህ ለአደጋ ተጋላጭነት በበረከተበት ዘመን እንኳን የባሕል ተወዳጅ መሰረት ያላትን ‘ባርቢን ሳይቀር ከንብሎ ከሽልማቶች ቁንጮ ጉብ አለ።
በሎስ አንጀለስ በሚገኘው የዶልቢ ቲያትር ትናንት እሁድ የተካሄደው የኦስካር ሽልማት የጋዛው እና የዩክሬኑ ጦርነቶች ከሰዎች ምናብ በማይለዩበት እናም የዩናይትድ ስቴትሱ ምርጫ በቅርብ ርቀት እየታሰበ ባለበት የተከናወ ነው።