ባይደን፣ ስለ ኢኮኖሚ አያያዛቸው፣ የሥነ-ተዋልዶ መብት፣ ሥደት እና በዩክሬን እና በጋዛ ስለሚካሄደው ጦርነት ያነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። የ81-ዓመቱ ባይደን፣ ንግግሩን ለሁለተኛ የሥልጣን ዘመን በአካል እና በአይምሮ ብቁ መሆናቸውንም ለማሳየት ይጠቀሙበታል ተብሏል። የአሜሪካ ድምፅ የዋይት ኃውስ ዘጋቢ አኒታ ፓውል ከዋሽንግተን ዲሲ ያደረሰችንን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
ባይደን ከጦርነት እስከ ኢኮኖሚ የሚዳስስሰውን ንግግራቸውን ዛሬ ምሽት ያደርጋሉ
Your browser doesn’t support HTML5
ዩናይትድ ስቴትስ ለምርጫ እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት 'ስቴት ኦፍ ዩኒየን' የተሰኘውን የአሜሪካንን የዛሬ ሁኔታ የሚዳስስ ዓመታዊ ንግግራቸውን ዛሬ ያደርጋሉ።