የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ሊገመገም ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ አፍሪካ - ፕሪቶርያ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል፣ ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር የተፈረመው ግጭትን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት አፈጻጸም፣ የስምምነቱ ፈራሚዎች እና አደራዳሪዎች በተገኙበት ይካሔዳል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ግምገማው እንደሚካሔድ አረጋግጠዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር፣ በግምገማው ላይ የሚሳተፉ ሲሆን፣ ዛሬ ኀሙስ ወደ አዲስ አበባ እንደሚያቀኑ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።