ባይደን እና ትረምፕ በ“ሱፐር ቲዩስዴይ” ቅድመ ምርጫ ቀንቷቸዋል

Your browser doesn’t support HTML5

- ኒኪ ሄሊ ከውድድሩ ወጡ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እና የቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ትላንት ማክሰኞ በበርካታ ግዛቶች በተካሄዱት “SUPER TUESDAY” ተብለው በሚጠሩት ቅድመ ምርጫዎች ወሳኝ ድሎች አግኝተው በመጪው ኅዳር ለሁለተኛ ጊዜ ለመፎካከር እየተቃረቡ ናቸው። የመጨረሻዋ የዶናልድ ትረምፕ ተቀናቃኝ ኒኪ ሄሊም ዛሬ ጠዋት የምረጡኝ ዘመቻቸውን አቋርጠው ከውድድሩ ወጥተዋል።

በትረምፕ አስተዳደር ዘመን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የነበሩት የ52 ዓመቷ ኒኪ ሄሊ የ77 ዓመቱ ትረምፕም ይሁኑ የ81 ዓመቱ ባይደን “በቀጣዮቹ አራት ዓመታት አሜሪካን ለመምራት ብቁ አይደሉም። መሪዎቻችሁን ከአዲሱ ትውልድ መምረጥ አለባችሁ” በማለት መራጮችን ሲያሳስቡ ቆይተዋል።

ይሁን እንጂ በርካታ ክሶች ያሉባቸው ዶናልድ ከፍተኛ የሪፐብሊካኖች ድጋፍ እንደያዙ ሲሆኑ ኒኪ ሄሊን ትናንት ቅድመ ምርጫ ካካሄዱት 15 ክፍለ ግዛቶች በ14ቱ አሸንፈዋቸዋል። ኒኪ ሄሊ የቬርሞንትን ድምጽ አግኝተዋል፡፡

የቪኦኤዋ የዋሽንግተን ዘጋቢ ካሮላይን ፕረሱቲ የትናንቱን ቅድመ ምርጫ “ሱፐር ቱስዴይ” እና ቀጣይ ሂደቶችን በተመለከተ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።