120 ቤተሰቦች በሰብአዊነት የተጣመሩበት የሕፃን ገሊላ ሕልም

Your browser doesn’t support HTML5

ዳላስ ከተማ የተወለደችውና ከአራት ዓመታት በፊት በ15 ዓመቷ በካንሰር ሕይወቷ ያለፈው ገሊላ መኮንን በሕይወት እያለች፣ ከ10 ዓመቷ ልጆችም መርዳት ይችላሉ በሚል ርእይ ከሁለት ጓደኞቿ ጋራ ሆና ኢትዮጵያ ላሉ ልጆች ርዳታን ትልክ ነበር። ይህን የምታደርገውም እርሷና ጓደኞቿ ለልደታቸው እና ለገና በዓል ከቤተሰቦቻቸው የሚያገኙትን ስጦታ በማጠራቀም ነው። ገሊላ ሕይወቷ ካለፈ በኋላ ቤተሰቦቿ የበጎ አድራጎት ድርጅት አቋቁመው ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋራ በመሰባሰብ 120 ቤተሰቦች ኢትዮጵያ የሚገኙ 120 ልጆችን በመርዳት ላይ ይገኛሉ።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።