አቶ በየነ ሰሎሞን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሠራተኞች ማህበር መስራች ናቸው። በማህበሩ ውስጥ ዋና ፀሃፊ እና ፕሬዝዳንት በመሆንም እንዲሁም የዓለም ስራ ድርጅት አስተዳደር ቦርድ አባል አና የዓለም ነፃ ሰራተኞች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል። የአፍሪካ ሠራተኞች ማህበር በአዲስ አበባ ሲመሰረትም ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት ነበሩ። የጡረታ ጊዜታቸው እሲክደርስ ደግሞ በአዲስ አበባ ዓለም ስራ ድርጅት፣ የአፍሪካ ቅርጫፍ ውስጥ ሰርተዋል።
በኢትዮጵ ሠራተኞች ማህበር ምስረታ እና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ጉልህ አስተዋፅኦ የነበራቸው አቶ በየነ በቅርቡ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ 95ኛ የልደት በዓላቸው ተከብሮላቸዋል ።
በ2004 "የኢትዮጵያ ሰራተኞች አንድነት ማህበር ውልደት፣ እድገት እና ውድቀት" በሚል በ2004 ስላሳተሙት መፅሃፍ እና በአጠቃላይ የህይወት እና የስራ ዘመናቸው ዙሪያ አሜሪካ ድምጽ አነጋግሯቸዋል፡፡