ኢትዮጵያውያን የዓድዋን ድል ትሩፋት ለማስቀጠል ችለዋል?

Your browser doesn’t support HTML5

የዓድዋ ድል፥ ኢትዮጵያውያን የአገራቸውን ነጻነት ለማስከበር ለመጀመሪያ ጊዜ “ብሔራዊ ሆነው” የተነሡበትና በኅብረት ተዋግተው ያሸነፉበት እንደሆነ፣ የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አየለ በከሪ ይገልጻሉ፡፡

“ድሉ በወቅቱ በጥቁር ሕዝብ ላይ የነበረውን እሳቤ እና ተረክ የቀየረ፣ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ምልክት ነው፤” የሚሉት ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጥናት እና ምርምር ማዕከል የታሪክ መምህር እና ተመራማሪ ዶክተር ደቻሳ አበበ ናቸው፡፡

ይሁንና የዓድዋ ድል፣ የአፍሪካውያንና የጥቁር ሕዝቦች ድል ምልክት ሆኖ እንዲዘከር በሚያስችል መልኩ ባለመሠራቱ ተገቢውን እውቅና አለማግኘቱን ያስረዳሉ፡፡

በቅርቡ የተመረቀው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አንድ ጥሩ ጅማሮ እንደሆነ ተመራማሪዎቹ በአብነት ይጠቅሱታል፡፡ በቀጣይም ድሉን በሚገባው ደረጃ እና ክብር ለመዘከርና የአፍሪካውያን የነጻነት አርኣያ ለማድረግ አብልጦ መሥራት እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።