ባሕር ዳር ዙሪያ እስከ ረፋድ ተኩስ ነበር - ነዋሪዎች

Your browser doesn’t support HTML5

በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕር ዳር ዙሪያ ዛሬ፣ ዐርብ እስከ ረፋድ የነበረውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ በከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ መቆሙን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የዐፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ወይም በተለምዶ “ዓባይ ማዶ” እና የዳግማዊ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ወይም በተለምዶ “ልደታ” ተብለው የሚጠሩ አካባቢዎች ዛሬ ከማለዳው አንሥቶ ከፍተኛ የከባድ መሣሪያ ድምፅ ሲሰሙ ማርፈዳቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የአማራ ክልል መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ “ክልሉ ውስጥ ሕግ የማስከበር ዘመቻ በተሟላ ሁኔታ እየተካሄደ ነው” ብሏል።

“የመከላከያ ሠራዊትና የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ባሕር ዳር ውስጥና በዙሪያው እያካሄዱት ነው” ባለው በዚህ ዘመቻ “ፅንፈኛ” ሲል የጠራውን ኃይል “ቤት ለቤት እያሰሱና እያፀዱት ናቸው” ብሏል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ባሕር ዳር ውስጥና በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው ፋኖ ታጣቂ ቡድን ቃል አቀባይ መሆናቸውን የገለፁልን አቶ መንግሥቱ አማረ የመንግሥቱን መግለጫ “ፕሮፓጋንዳ ነው” ሲሉ አጣጥለውታል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።