በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ አካባቢዎች የሚፈጸሙ የእገታ እና የግድያ ተግባራት፣ “የዜጎችን እንቅስቃሴ ገድበዋል፤” ያለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ/ኢሰመጉ/፣ መንግሥት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቋል፡፡
የሰብአዊ መብቶች ተቋሙ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ፣ ከዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የተወሰዱ አራት መነኰሳት አባቶች እና በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ አካባቢ ስድስት ሲቪሎች ሰሞኑን በታጣቂዎች መገደላቸውን አስታውሷል፡፡
ምክትል ዋና ዲሬክተሩ አቶ ተስፋዬ ገመቹ፣ መንግሥት ለመሰል የእገታ እና የግድያ ተግባራት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡
በተያያዘ፣ ከደብረ ብርሃን እስከ ደሴ ከተሞች ያለው የየብስ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደተቋረጠ መቀጠሉን አስተያየት ሰጪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።