የኬኒያ መንግሥት የኑሮ ውድነቱን ለማቅለል ርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

የኬኒያ መንግሥት፥ ግብር በብዛት በመሰብሰብ፣ የመንግሥትን ወጪ በመቀነስ ምጣኔ ሀብቱን ለማጠናከር እንደተነሣ አስታወቀ፡፡ ኬኒያ “ዕዳዎቿን እየከፈለች በዐቅሟ እንድትኖር ለማድረግም እሠራለሁ፤” ብሏል፡፡

የአገሪቱ መንግሥት ይህን የተናገረው፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እ.አ.አ በዘንድሮ 2024 ትንበያው፣ ኬኒያንና ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ አገሮች፣ የሸቀጦች ዋጋ መናር ሕዝባዊ ዐመፅ ሊያሥነሳ እንደሚችል ሰሞኑን ማስጠንቀቁን ተከትሎ ነው፡፡

መሐመድ ዬሱፍ ከናይሮቢ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።