በግዳጅ ደመወዝ የተቆረጠባቸው የጂንካ ከተማ መምህራን አስተዳደሩን አማረሩ

Your browser doesn’t support HTML5

የጂንካ ከተማ አስተዳደር መምሕራን ለልማት በሚል የደመወዛቸው ግማሽ እንደተቆረጠባቸው ገልፀው ቅሬታ አሰሙ። ከ600 በላይ መምህራን ከጥር ወር ደመወዛቸው ላይ የተቆረጠው ፈቃደኝነታቸው ሳይጠየቅ እንደኾነ የዞኑ መምህራን ማኅበር ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው ገለቱ ለቪኦኤ ተናግረዋል። የጂንካ ከተማ አስተዳደር ደሞዛቸው የተቆረጠው ውይይት ከተደረገ በኋላ ነው ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።