ከፋኖ ታጣቂዎች ጋራ የሰላም ንግግር እንዲጀመር ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ መንግሥትን ጠየቀች

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሱት የፋኖ ታጣቂዎች መካከል ንግግር እንዲጀመር፣ ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋራ የተደረገው ንግግር ደግሞ እንዲቀጥል፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥያቄ ማቅረቧን አስታወቀች።
ዩናይትድ ስቴትስ፣ ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋራ የተጀመረው ንግግር እንዲቀጥል ኹኔታዎችን ለማመቻቸት ዝግጁ መኾኗንም፣ የአገሪቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ቆይታ ያደረጉት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ እና አምባሳደር ማይክ ሐመር፣ ዛሬ በበይነ መረብ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።