የቱርክ እና የአሜሪካ ግንኙነት በፍጥነት እየተሻሻለ በመሆኑ፣ አናካራ F-35 ወታደራዊ ጄቶችን እንድትገዛት ዋሽንግተን ሃሳብ አቅርባለች፡፡ በልዋጩ ግን ቱርክ ከሩሲያ የገዛቻቸውን S-400 ፀረ አውሮፕላን ሚሳዬሎችን ወደ ሦስተኛ አገር እንድታስተላልፍ አሜሪካ ትሻለች፡፡
የቪኦኤው ዶሬን ጆንስ ከኢስታንቡል እንደላከው ዘገባ ከሆነ፣ S-400 ፀረ አውሮፕላን ሚሳዬሎች አንካራ እጅ መግባታችው፣ በቱርክ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ሥር የሰደደ ግንኙነት አመልካች ነው።