በሰሜን ሸዋ ዞን በቀጠለው ግጭት ሰዎች ተገደሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደጋም ወረዳ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በነበረው የተኩስ ልውውጥ፣ ሦስት ሰዎች መገደላቸውንና ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ።

በአንጻሩ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በፌስቡክ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው፣ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ምሥራቅ ጉጂ ዞኖች ውስጥ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሔደ ነው። በሰሜን ሸዋ ዞን ስላለው ግጭት ግን ሚኒስቴሩ የጠቀሰው ነገር የለም፡፡ ከሰሜን ሸዋ ዞንና ከደጋም ወረዳ ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረትም ለጊዜው አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።