ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ትንታኔ ተቋም መሥራቿ ኢትዮጵያዊት

Your browser doesn’t support HTML5

ራሔል ቡን ደጀኔ፣ ከአዳጊነት ዕድሜዋ አንሥቶ ነዋሪነቷ በኔዘርላንድ ነው፡፡

የአምስት ልጆች እናት የኾነች ራሔል ቡን፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ላሉ የእግር ኳስ ፌደሬሽኖች፣ እንዲሁም እንደ አያክስ አምስተርዳም እና ማንችስተር ዩናይትድ ባሉ ግዙፍ የስፖርት ክለቦች አገልግሎት ላይ የሚውለው፤ በባለሞያ የተደገፈ የስፖርተኞች አቋምንና የጨዋታ ትንታኔዎችን የሚያቀርበው የ“አርኤንዲ ግሩፕ” ተቋም መሥራች፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ሥራ ፈጣሪ ናት።

ተቋሟ፣ ባለፉት 15 ዓመታት ለስድስት ሺሕ ሰዎች የሥራ ዕድል እንደፈጠረ ለአሜሪካ ድምፅ አጋርታለች። በተጨማሪም “ሼር” በተሰኘ መርሐ ግብር አማካይነትም፣ በአነስተኛ እና ጥቃቅን የንግድ ዘርፍ ውስጥ ለተሰማሩ ነጋዴዎች፥ በአቅም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ሥልጠናና በተለያዩ ምክሮች ልገሳ ላይ በመሥራትም ትገኛለች።

ከራሔል ቡን ደጀኔ ጋራ ቆይታ አድርገናል።