የሰሜን ግጭቶችና መፍትኄ፤ ፋኖና ሌሎች

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ መንግሥት አማራ ክልል ውስጥ በበረታው የፀጥታ መስተጓጎል ምክንያት ለስድሥት ወራት ጥሎት የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ በአራት ወራት አራዝሞታል።

ክልሉ ውስጥ ከፌደራል ኃይሎች ጋር የተካረሩ ግጭቶች ውስጥ ያሉት የፋኖ ታጣቂዎች ትግራይ ውስጥ ለሁለት ዓመታት በተካሄደው ጦርነት ወቅት ዛሬ ከተናነቋቸው የመከላከያ ኃይሎች ጋር ተሰልፈው ተዋግተዋል።

ወጥ ሆኖ የተማከለ የፋኖ አመራር ስለመኖሩና የተጠሪነቱ ሠንሰለት ምን እንደሚመስል በውል ባይታወቅም ጎጃም ውስጥ ይንቀሳቀሳል ያሉትና “የአማራ ህዝባዊ ኃይል - ፋኖ እንደሚባል የተናገሩት ቡድን የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ እንደሆኑ የገለፁት፣ አስረስ ማረ ዳምጤ እባላለሁ ያሉ ሰሞኑን ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።

ያነጋገራቸው ዘጋቢያችን ከፌደራልና ከትግራይ ባለሥልጣናት ማብራሪያዎችን ለማግኘት ያደረገውን ጥረት አካትቶ ተከታዩን አዘጋጅቷል።