በጣልያን ወረራ ወቅት ለሰባት ወራት ለኢትዮጵያ መንግሥት መቀመጫ ሆና ያገለገለችውና በሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የንግድ መዳረሻ የነበረችው ጎሬ ከተማ፣ አሁን ላይ ብዙ ታሪኮችን እንደያዘች መረሳቷን ነዋሪዎቿ ይናገራሉ።
ጎሬ ከተማ ወደ 22 ሀገር አቀፍ ቅርሶችን በፌደራል ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ማስመዝገቧን የጠቀሱት፣ የኢሉ አባቦር ዞን ባህል እና ቱሪዝም ታሪክ አጥኚ አቶ ተመስጌን ኮርጄ ገለታ ደግሞ፤ ከተማ ትኩረት እንድታገኝ እየተሠራ እንደሆነ አመልክተዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።