በአዋሽ አርባ የቆዩ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ እስረኞች ወደ አዲስ አበባ ተዛወሩ

Your browser doesn’t support HTML5

የሕዝብ እንደራሴዎችን ጨምሮ ወደ አዋሽ አርባ ተወስደው የነበሩ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ እስረኞች፣ ወደ አዲስ አበባ እንደተዛወሩ ለአሜሪካ ድምፅ የገለጹት ጠበቃቸው፣ ሆኖም ደንበኞቻቸውን ለማግኘት እንዳልተፈቀደላቸው ተናግረዋል።

እስረኞቹ ወደ አዲስ አበባ መዛወራቸውን ከቤተሰቦቻቸው እንዳረጋገጡ የጠቀሱት፣ ከጠበቆቻቸው አንዱ የኾኑት አቶ ሰሎሞን ገዛኸኝ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ እስረኞቹን በአካል ለማግኘት ሞክረው እንደተከለከሉ አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ፣ እስረኞቹን ለማግኘት ከፖሊስ ጋራ እየተነጋገረ እንደኾነና በቅርቡም እንደሚያገኛቸው ጠቁሟል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከ“ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ” ውድድር ጋራ በተገናኘ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ወጣቶች እንደተለቀቁ፣ ጠበቃቸው ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል፡፡