በሐዲያ ዞን 22 ሕፃናት በኩፍኝ ወረርሽ ሕይወታቸው አለፈ

Your browser doesn’t support HTML5

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሐዲያ ዞን ሾኔ ከተማ በተከሠተ የኩፍኝ ወረርሽኝ፣ የ22 ሕፃናት ሕይወት እንዳለፈ፣ የዞኑ ጤና መምሪያ እና ሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስታወቁ።

ከ500 በላይ ሕፃናት በወረርሽኙ እንደተያዙና የተወሰኑቱ አሁንም በጤና ተቋማት ሕክምና እየተከታተሉ እንደሆኑ፣ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ ታከለ ኦርኔሞል ገልጸዋል።

ወረርሽኙ፣ ባለፈው ታኅሣሥ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. እንደተከሠተ የተናገሩት ኃላፊው ፣ ሞት የተመዘገበው ባለፈው ሳምንት ውስጥ ነው፤ ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።