የአካባቢው ሰላም እና ጸጥታ ጥበቃም፣ ከወረዳው እና ከዞኑ አቅም በላይ እንደኾነ አክለው የገለጹት ኃላፊው፣ የፌደራል መንግሥቱን ጣልቃ ገብነት ጠይቀዋል።
ጥቃቱ ባስከተለው አለመረጋጋት የአካባቢው መደበኛ እንቅስቃሴ እንደተገደበም፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ለጥቃቱ ተጠያቂ ከተደረገው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ቃል አቀባይ፣ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ፋይል ያገኛሉ)