ትረምፕ ለዩክሬን እና ለእስራኤል የሚፈቀደው እርዳታ ስምምነት እንዳይቋጭ እንቅፋት እየሆኑ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በመጪው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲው ዕጩ እንደሚሆኑ የሚጠበቁት የቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ የውጭ ርዳታ እንዲለቀቅ እና የኢሚግሬሽን ደንቦች እንዲጠብቁ የሚያደርገው ስምምነት ዳር እንዳይደርስ ሊያደናቅፉ ተነስተዋል፡፡

ለዩክሬን ለእስራኤል እና ለታይዋን ድጋፍ የሚውል የ106 ቢሊዮን ዶላር የውጭ እርዳታ የሚያስፈቅደው እና የሀገሪቱን የኢሚግሬሽን ደንቦች የሚያጠብቀውን ስምምነት ለመቋጨት ኋይት ሐውስ እና የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ዲሞክራት እና ሪፐብሊካን አባላት ለወራት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

የቪኦኤ የኋይት ሐውስ ቢሮ ዋና ዘጋቢ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ያጠናቀረችውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ታቀርበዋለች፡፡