ለዳሰነች ልዩ ወረዳ የጎርፍ ተፈናቃዮች የተቀናጀ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳሰነች ልዩ ወረዳ፣ የኦሞ ወንዝ ሙላት ባስከተለው ጎርፍ ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች የሚቀርበው ድጋፍ የተቀናጀ እንዲኾን፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጥሪ አቅርቧል።

ማኅበሩ፣ የ44 ሚሊዮን ብር ያህል ድጋፍ እንዳደረገም አስታውቋል። የልዩ ወረዳዋ ተፈናቃይ አርብቶ አደሮች ተወካዮች ደግሞ፣ እየቀረበ ያለው ድጋፍ በቂ እንዳልኾነና ከፍተኛ የውኃ እጥረት መኖሩን አመልክተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡