በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ አካባቢዎች የሚካሔዱ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች፣ በእንቅስቃሴው ላይ ጫና እንዳሳደሩበት ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬ ሕይወት ታምሩ፣ የኩባንያውን የግማሽ ዓመት የክንውን ሪፖርት፣ ዛሬ ይፋ ሲያደርጉ እንደተናገሩት፣ በግጭቶች ምክንያት የተፈጠረ የአገልግሎት መቋረጥ፣ የገበያ አለመረጋጋት፣ በኔትወርክ ሀብት ላይ የሚደርሱ አደጋዎች እና ሌሎችም ችግሮች፣ በሥራ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ጫና አሳድረዋል፡፡
ይህም ኾኖ ኩባንያው፣ በመንፈቅ ዓመቱ ከፍተኛ አፈጻጸም እንዳሳየና የ11 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ እንዳገኘ ገልጸዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡