ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች “የመረጃ ነፃነት አዋጅን” አያከብሩም ተባለ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ላይ ባካሔደው የመልካም አስተዳደር አፈፃፀም ምዘና፣ አብዛኞቹ የመረጃ ነፃነት ዐዋጅን እንደማያከብሩ እና ለብዙኃን መገናኛ መረጃ እንደማይሰጡ ማረጋገጡን አስታወቀ፡፡

የምዘና ጥናቱን በማስመልከት ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት፣ የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ሐላፊ አቶ አዳነ በላይ፣ በምዘናው ከተካተቱት 15 ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች መካከል፣ በ12ቱ ላይ ይህ ችግር መታየቱን ጠቅሰዋል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶቹ፣ ከግልፀኝነት፣ ፍትሀዊነትና ከሕግ ጋራ የተያያዙ ችግሮችም እንዳሉባቸው ሐላፊው አመልክተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የጋዜጠኝነትና መምህር ዶር. ጌታቸው ድንቁ፣ መረጃን ለብዙኃን መገናኛ ተደራሽ አለማድረግ፣ አሳሳቢ ችግር እየሆነ መምጣቱን ተናግረው፣ ማህበራዊ ተፅዕኖው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡