“የምግብ ዋጋ መናር ህይወታችንን እየፈተነ ነው” ሸማቾች

Your browser doesn’t support HTML5

የምግብና ምግብ ነክ ምርቶች ዋጋ ጭማሪ ህይወታቸውን እየፈተነው እንደሚገኝ ሸማቾች ተናገሩ። የአንዳንድ ምርቶች ዋጋ በአንድ ዓመት ውስጥ እስከ እጥፍ እንደጨመረ ሸማቾችና ችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ የምግብ እህል ምርታማነት ከፈረንጆቹ 2014 ማለትም ከዛሬ 10 ዓመት ወዲህ ጀምሮ እየቀነሰ ነው የሚሉት የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የሰላም እጦትና የእንቅስቃሴ ገደቦች መብዛትም ለዋና ንረቱ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዳበረከቱ ያስረዳሉ።

በመፍትሔነት በሀገሪቱ ሰላም ማስፈን እና አጠቃላዩን አገራዊ ምጣኔ ሐብት ማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ በምክረ ሃሳብነት ቀርበዋል። አሁን ባለው ሁኔታ ከተቀጠለ ግን መጪው ዓመት የከፋ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎቹ ያስጠነቅቃሉ።

የተያያዘውን ፋይል ያድምጡ፡፡