ስምምነቱ በቀጣናው ሊኖረው የሚችለው ተጽዕኖ - የተንታኞች አስተያየት

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መሪዎች የተፈረመው ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበት የመግባቢያ ሠነድ ሶማሊያን ጨምሮ ከሌሎች ጎረቤት ሃገሮች ጋር ባላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል በአሜሪካ ኢንዲያና ዩንቨርስቲ የህገ መንግስታዊ ዲሞክራሲ ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት አቶ አለማየሁ ፋንታው ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡፡

“ስምምነቱ የኢትዮጲያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ የሚሆነው ብስለት ያላቸው ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን መስራት ከተቻለ ብቻ ነው” ሲሉም አክለዋል፡፡

የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ክቡር ገና በበኩላቸው “እንደ አየር መንገድ ያሉትን ትላልቅ ሃገራዊ ተቋማት የስምምነቱ አካል ማድረግ በቂ ዉይይት የሚጠይቅ ነው” ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የመግባቢያ ስምምነቱን የተቃወመው ሶማሊያ መንግስት በኢትዮጵያ የሚገኙትን አምባሳደሩን ጠርቷል፡፡