በአዲስ አበባ በተደራጀ ዝርፊያና ሌሎች መሰል ወንጀሎች የተጠረጠሩ ታሠሩ

Your browser doesn’t support HTML5

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከአዲስ አበባ ፀጥታ ዘርፍ ጋር በመቀናጀት ለተከታታይ 20 ቀናት አካሄድኩት ባለው "ልዩ ኦፕሬሽን" በተደራጀ ዝርፊያና ድብደባ እንደዚሁም በሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ ከ 5,500 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።

እንቅስቃሴው “ለከተማዋ ነዋሪዎች ምሬት ምላሽ ለመስጠት እንደዚሁም እየተበራከቱ የመጡትን የተለያዩ ወንጀሎች በእንጭጩ ለመቅጨት የተካሄደ ነው” ሲሉ የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አድማሱ ኢፋ ገልፀዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በከተማዋ የስርቆትና የዕገታ እንደዚሁም ሌሎች ወንጀሎች እየተበራከቱ መኾናቸውን አመልክተዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የሚውሉበት መንገድ ህጋዊ ሂደትን የተከተለ ስለመሆኑ ጥያቄ የሚያነሱም አሉ፡፡ ከወንጀለኞች ጋር በማበር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ የፀጥታ አካላትም እንዳሉ ተመልክቷል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡