ምሁራን የየመን ሁቲ ታጣቂዎች የቀይ ባሕር ላይ ጥቃት በጥንቃቄ እንዲታይ አሳሰቡ

Your browser doesn’t support HTML5

የየመን ሁቲ ታጣቂዎች፣ በቀይ ባሕር አካባቢ በሚያልፉ መርከቦች ላይ እያደረሱ ያሉት ጥቃት፣ የእስራኤል ሐማስ ጦርነት ቅጥያ ተደርጎ ይታያል፡፡

ይኸው ጥቃት በቀጠለ ቁጥር፣ ቀጣናው፥ “ዐዲስ ስጋቶችን እንዲያስተናግድ ያደርገዋል፤” ሲሉ፣ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር እና ተመራማሪ የኾኑት ሱራፌል ጌታሁን ይናገራሉ፡፡

ክሥተቱ፣ በቀጣናው፥ “የኀይል አሰላለፍ መዘበራረቅ አስከትሏል፤” የሚሉት ደግሞ፣ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የመካከለኛው ምሥራቅ ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር ሙሐመድ ሰይድ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ የቀጣናው ሀገራት፣ ለየትኛውም አካል ሳይወግኑ ኹኔታውን በጥንቃቄ ሊያዩት እንደሚገባ፣ ዶክተር መሐመድ አክለው ይመክራሉ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡