የልጅነት ሕልሙን እየኖረ ያለው የሙዚቃ አቀናባሪው መዳረሻውን ይናገራል

Your browser doesn’t support HTML5

ተወዳጁ የሙዚቃ አቀናባሪ ኪሩቤል ተስፋዬ፣ የመጀመሪያውን አልበም ያቀናበረው በዐሥራዎቹ መጨረሻ ዕድሜው ነው፡፡

የአብሮ አደጉ እና የጓደኛው ኄኖክ አበበ የመጀመሪያ አልበም ቅንብር፣ ለሙከራ የሠራው ነበር፡፡ እርሱ “ሙከራ ነበር” ቢለውም ባልጠበቀው መልኩ፣ በታዋቂ አቀናባሪ ከተወደደለት በኋላ ወደ ሞያው በሰፊው እንደገባ ኪሩቤል ይገልጻል፡፡

ከዚያን ጊዜ ወዲህ፣ በቁጥር የማያስታውሳቸው የብዙ ነጠላ ዜማዎችንና በርካታ አልበሞችን አቀናብሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የኖቤል የሰላም ሽልማት በተቀበሉበት ዝግጅት እና በሌሎችም በርካታ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይም ተጫውቷል፡፡

ኪሩቤል ለሙዚቃው ዓለም የተማረከው ገና በልጅነቱ እንደነበር ያወሳል፡፡ በዳህላክ ባንድ ውስጥ በዋናነት ድራመርነት፣ ለብዙ ዓመታት የሠሩትን ሙዚቀኛ አባቱ በአርኣያነት እያየ የሙዚቃ ፍቅሩን አጎልብቷል፡፡ ኾኖም ይህ ሩቅ ያለመበት ሕልሙ በቤተሰቡ አልተወደደለትም ነበር፡፡

ወጣቱ አቀናባሪ ኪሩቤል፣ እነዚኽን ፈተናዎች እንደምን አልፎ የሕይወት ዘመን ጉዞውን ቀጠለ? ነገስ የት መድረስ ይፈልጋል? መልሱን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡