የተጓተተው የላሊበላ አብያተ ክርስቲያን ጥገና ጉዳታቸውን እንዳያባብሰው አስግቷል

Your browser doesn’t support HTML5

በዐማራ ክልል በተቀሰቀሰው የጸጥታ መደፍረስ ምክንያት፣ በፈረንሳይ መንግሥት ሊካሔድ የነበረው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን የጥገና እና ጥበቃ ሥራ እንደተስጓጎለ፣ የከተማ አስተዳዳሩ የባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የጥገናው መጓተት፣ አብያተ ክርስቲያኑ ያሉበትን የጉዳት ደረጃ እንደሚያባብሰው ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

የቱሪዝም ፍሰቱም በጸጥታው ችግር እንደታወከ፣ የከተማዋ አስጎብኚዎች እና የሆቴል ባለንብረቶች ማኅበራት ይናገራሉ፡፡ ከአስጎብኚዎቹም ጥቂት የማይባሉት፣ በችግሩ ምክንያት ልመናን ጨምሮ ለከፋ ማኅበራዊ ጉስቁልና እንደተዳረጉ፣ ማኅበራቱ ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ የሆቴል ባለንብረቶቹ፣ በሚሊዮኖች ተበድረን የገነባነው ሆቴል፣ በአገልግሎት መቋረጥ ሳቢያ ለኪሳራ እንዳደረሳቸውና ከአምስት ሺሕ በላይ ሠራተኞችን ለማሰናበት እንዳስገደዳቸው አክለው አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።