በግንደበረት የግጭት ተፈናቃዮች በካቺሲ ከተማ ድጋፍ እየተጠባበቁ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የግንደ በረት ወረዳ አስተዳደር፣ በመንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል በቀጠለው ግጭት፣ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮተፈናቅለው በካቺሲ ከተማ የሚገኙ ከ10ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች፣ ሰብአዊ ድጋፍ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ገልጿል፡፡

የካቺሲ ከተማ ከንቲባ አቶ ተፈራ ዶቆሳ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በወረዳው የተለያዩ አካባቢዎች፣ ሸኔ ሲሉ የጠሩትን ታጣቂ ሸሽተው ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ዜጎች፣ በከተማው ተበታትነው እየኖሩ እንዳሉ አመልክተዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎችም፣ በተለይ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ይንቀሳቀስበታል ባሉት ቆላማ አካባቢ፣ ሕዝቡ በመንግሥትም በታጣቂውም ችግር እንደሚደርስበትና ቀዬውን ጥሎ ለመሸሽ እንደተገደደ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።