በኢትዮጵያ ነክ ዘገባዎች ስማቸውን የማይገልጹ መረጃ ሰጭዎች እየበዙ ስለመምጣታቸው ባለሞያዎች ይናገራሉ

Your browser doesn’t support HTML5

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ ኢትዮጵያን በሚመለከቱ የአገር ውስጥ እና የውጭ ብዙኀን መገናኛዎች የሚወጡ ዘገባዎች፥ ስማቸው እንዲገለጽ፣ ድምፃቸው እንዳይሰማም ኾነ ምስላቸው እንዳይታይ በሚፈልጉ መረጃ ሰጭዎች የተሞሉ እንደኾኑ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ጋዜጠኞች እና የብዙኀን መገናኛዎች ሓላፊዎች ተናግረዋል፡፡

የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የንግድ ማኅበረሰብ አባላት፣ ባለሞያዎች እና ተራ ዜጎች፣ ስማቸው እንዲገለጽ ያለመፍቀዳቸው ነገር እየበዛ እንደኾነ፣ በሥራቸው አጋጣሚ እንደታዘቡ፡- በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮምዩኒኬሽን ትምህርት ቤት መምህር መኩሪያ መካሻ፣ የኢትዮጵያ አርታዕያን(ኤዲተሮች) ማኅበር መሥራች እና የቦርድ ጸሐፊ እና የሳምንታዊ እንግሊዝኛ ጋዜጣ ካፒታል ኤዲተር ሙሉቀን የወንድወሰንና የኤቢኤስ ቴሌቪዥን ከፍተኛ ሪፖርተር ኤርምያስ በጋሻው ይናገራሉ፡፡