ለኬንያውያንንና ለቻይናውያን ትስስር ኤምባሲው የደገሰው ማዕድ ቅሬታውን ያረግበው ይኾን?

Your browser doesn’t support HTML5

ኬንያ ከቻይና ጋራ ያላትን የንግድ እና የብድር ግንኙነት አስመልክቶ፣ የኬንያውያን ክርክር ተጋግሎ ቀጥሏል፡፡

በናይሮቢ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ፣ በሰፊው እየደገሰ በመጋበዝ፣ ኬንያውያን ከቻይናውያን ጋራ ያላቸውን ባህላዊ ትስስር ለማጎልበት ጥረት በማድረግ ላይ ነው፡፡

የሁለቱ አገሮች ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ሚዛን ያጋደለ እንደኾነ የሚናገሩት ተንታኞች ደግሞ፣ የኤምባሲው ጥረት፣ ኬንያውያን የሚያሰሙትን ቅሬታ ለማርገብ የታለመ ነው፤ ይላሉ፡፡

ቪክቶሪያ አሙንጋ ከናይሮቢ ተጨማሪ አላት፡፡ ቆንጅት ታየ ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች፡፡