በድንበር ደኅንነት ስምምነት ባለመኖሩ ለዩክሬን የሚሰጠው ርዳታ ደንቃራ ገጥሞታል

Your browser doesn’t support HTML5

ዩክሬን፣ በሩሲያ ወረራ ምክንያት ያለባትን ጦርነት ለመደገፍ፣ በዋይት ሐውስ እንዲሰጥ የታቀደውን 60 ቢሊዮን ዶላር አስመልክቶ፣ የአሜሪካው ሸንጎ በቂ የይኹንታ ድምፅ ይኖረው እንደኹ ለመፈተሽ፣ ዛሬ የሙከራ ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የቪኦኤ የኮንግረስ ዘጋቢ ካትሪን ጊብሰን እንደላከችው ጥንቅር ከኾነ ግን፣ በሴኔቱ ያሉ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት፣ ለዩክሬን ሊሰጥ ለታሰበው ገንዘብ የድጋፍ ድምፅ የሚሰጡት፣ በፈንታው፥ የአገሪቱን የድንበር ደኅንነት አስመልክቶ እንዲወጣ የሚሹት ሕግም ተቀባይነት ከአገኘ ነው።

ዘገባውን እንግዱ ወልዴ ወደ ዐማርኛ መልሶታል፡፡