ኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች 56 ሰዎች እንደተገደሉ ኢሰመኮ አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ)፣ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ፣ በዐማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ እና በኦሮሚያ ክልሎች፣ በሲቪል ሰዎች ላይ እየተፈጸመ ነው ያለው ጥቃት፣ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ገልጿል፡፡

እንደተቋሙ መግለጫ፣ ባጋመስነው የኅዳር ወር ውስጥ ብቻ፣ በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች፣ በሲቪሎች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች፣ በትንሹ 56 ሰዎች ሲገደሉ፤ በዐማራ ክልል ደግሞ በቁጥር ያልተጠቀሱ ዐያሌ ሰዎች እንደተገደሉ አመልክቷል፡፡

ጥቃቶቹ ማንነት ተኮር እንደኾኑም የገለጹት፣ የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ሥራ ክፍል ከፍተኛ ዲሬክተር ዶር. ሚዛኔ አባተ፣ ችግሩ አፋጣኝ ፖለቲካዊ እልባት እንደሚሻ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።